Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dds

Department on Disability Services
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about Department on Disability Services for Amharic speakers.

የኤጀንሲው ስም:- የአካል ጉዳተኝነት አገልግሎቶች መምሪያ (DDS)      
ተልዕኮ:-
የአካል ጉዳተኝነት አገልግሎቶች መምሪያ (DDS) ተልዕኮ በእያንዳንዱ የኮሎምብያ ዲስትሪክት አካባቢ ለሚገኙ የአካል ጉዳተኛ ሰዎች በቤተሰቦቻቸው፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሥራ ቦታዎች እና በማህበረሰቦቻቸው ውስጥ አስፈላጊ ዓባሎች እንደመሆናቸው የተሟላ እና ውጤታማ ህይወት መምራት የሚያስችሉ ዘመናዊ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው አገልግሎቶችን መስጠት ነው።

ገለጻዎች እና አገልግሎቶች:-
የእድገት ጉዳተኝነቶች አስተዳደር (DDA) በኮሎምብያ ዲስትሪክት ውስጥ ብቁ ለሆኑ የእዕምሮ እና የእድገት ጉዳተኛ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን እና ድጋፎችን የመቆጣጠር እና የማስተባበር ኃላፊነት አለበት።   “DDA” ከ2100 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የቤት እና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በማቀነባበር እያንዳንዱ ሰው በመረጠው መኖር፣ መስራት እና በማህብረሰብ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ ከመቻሉ ባሻገር ጤናን፣ ደህንነትን እና ጥራት ያለው ህይወትን ያበረታታል።

የመልሶ ማቋቋም አገልግሎቶች አስተዳደር (RSA) የአካል፣ የእዕምሮ እና የስሜት ጉዳተኝነቶች ያለባቸው ሰዎች ሥራ በመያዝ እና በሥራ ላይ በመቆየት፣ በኢኮኖሚ ራስን መቻል እና ነጻነትን በማግኘት የበለጠ ጥራት ያለው ህይወት እንዲመሩ ይረዳል።  ለዓይነስውራን እና ማየት ለተሳናቸው አገልግሎት የሚሰጡ የRSA ሠራተኞች ለዲስትሪክቱ ዓይነስውራን እና ማየት ለተሳናቸው ኗሪዎች ዕድሎቻቸውን የሚያሰፉ አገልግሎቶችን በመስጠት ትክክለኛ ምርጫ እንዲያደርጉ አስፈላጊ መረጃዎችን ያቀርባል።
የጉዳተኝነት መገምገሚያ ክፍል (DDD) የሶሻል ሴኩሪቲ የጉዳተኝነት ኢንሹራንስ (SSDI) እና ተጨማሪ የደህንነት ድጎማ ገቢን (SSI) ከፌደራል ሶሻል ሴኩሪቲ አስተዳደር ጋር በመሆን ይወስናል እንዲሁም ያስተዳድራል።

አገልግሎቶች:-
የእድገት ጉዳተኝነት አስተዳደር – ለ”DDA” አገልግሎቶች እባክዎ ወደ ማመልከቻ እና የብቁነት ክፍል  በ“202-730-1791” ይደውሉ።

የማገገሚያ አገልግሎት አስተዳደር – ለ”RSA” አገልግሎቶች ለማመልከት እባክዎ ወደ የRSA ማመልከቻ ቢሮ በ“202-442-8400” ይደውሉ።

የጉድለት መገምገሚያ ክፍል – የ”SSDI” እና  “SSI”ን በተመለከተ እባክዎ በ”202-442-8500” ይደውሉ።  

የማስተርጎም አገልግሎቶች:
በስልክ ወይም በአካል ቢሮአችንን ሲጠይቁ፣ በቋንቋ አገልግሎት የማግኛ መስመር አማካኝነት አስተርጓሚ እንዲያገኙ የሥራ ባልደርባችን በደስታ ያገናኝዎታል።  በተጨማሪም የምናገለግላቸውን ሰዎች ፍላጎት ለማሟላት ጉዳተኛ ለሆኑ ሰዎችን እንደ “ASL” ዓይነት የማስተርጎም እርዳታ እንሰጣለን።፡፡  

አድራሻችን:-

Department on Disability Services (DDS)
250 E Street, SW
Washington, DC 20024
(202) 730-1700